Simeon mountains in Ethiopia, Africa

ድሬዳዋ

ሱንካሳ የጎርፍ አደጋ ስጋትን፣ የአፈር መሸርሸርንና የከተማ ውሃ እጥረትን ለመቅረፍ በድሬ ዳዋ የደቻቱ ወንዝ ተፋሰስን የማደስ ሥራ የሚያከናውን ይሆናል። ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች የሚኖሩ ከ200,000 በላይ ሰዎች ሥርዓተ-ጾታን ማእከል አድርገውና ተፈጥሮ ላይ ተመሥረተው ከሚወሰዱት የመፍትሔ እርምጃዎች ተጠቃሚ ይሆናሉ። የደን ልማት ማከናወን፣ ጥብቅ የደን ጣቢያዎችን ማቋቋም፣ ተፋሰሶችን ማስተዳደር፣ ዘላቂ መተዳደሪያ ማስገኘትና የከተማ ዛፍ ተከላ ማከናወን የነዚህ እርምጃዎች አካል ሲሆኑ የጎርፍና የሙቀት ተጽእኖዎችን ለመቀነስ የሚያግዙ ይሆናል።

የጎርፍ መጥለቅለቅ፣ የአፈር መሸርሸርና የውሃ እጥረት በድሬ ዳዋ የሚስተዋሉ የአየር ንብረት ለውጥ አሳሳቢ ስጋቶች ናቸው። የከርሰ ምድር ውሃ እየቀነሰ በመምጣቱ የማኅበረሰቡ ጤናና የአካባቢው ኢኮኖሚ የሙቀትና የውሃ እጥረት ስጋት አንዣቦባቸዋል።

ሱንካሳ ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች በሚገኙ የከተማና የገጠር ቀበሌዎች (መንደሮች) ላይ በማተኮር ተፈጥሮ ላይ የተመሠረቱ መፍትሔዎችን ተግባራዊ ለማድረግ ከአገር ውስጥ ተዋናዮች ጋር በመተባበር ይሠራል። በሱንካሳ ስር የሚተገበሩት ተፈጥሮ ላይ የተመሠረቱ መፍትሔዎች የጎርፍ መጥለቅለቅንና የአፈር መሸርሸርን ይቀንሳሉ፣ የከርሰ ምድር ውሃ ክምችትንና የጥብቅ ደን ጣቢያዎች ልማትን ያሳድጋሉ እንዲሁም የግብርናና ደን ልማት ዕድሎችን በማስፋት የመሬት ምርታማነት፣ የሰብል ምርትና የቴክኖሎጂ ተደራሽነት እንዲሻሻል ያደርጋሉ።

ይህ ዕቅድ በችግኝ አመራረት፣ በንብ እርባታ፣ በመኖ ልማት፣ በኮምፖስት አመራረትና ሌሎች ከፕሮጀክቶች ጋር በተያያዙ ዘርፎች ላይ የአቅም ግንባታ ሥልጠናና የሥራ ዕድል በመስጠት ከ3,500 እስከ 4,000 ሰዎችን በቀጥታ ተጠቃሚ ያደርጋል። ፕሮጀክቱ የማኅበረሰብ ፓርኮችን በማልማትና በሕዝብ መሬቶች፣ በግል ይዞታዎችና በመንገድ ዳሮች ላይ ዛፎችን በመትከል የከተማ አረንጓዴ ቦታዎች እንዲስፋፉ ያበረታታል።

ሱንካሳ በደቻቱ ወንዝ ተፋሰስ ላይ የሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች

SUNCASA Dire Dawa Watershed Vertical