Nyabarongo River in Kigali, Rwanda

ኪጋሊ

ሱንካሳ በኪጋሊ ሩዋንዳ የጎርፍ አደጋን፣ የመሬት መንሸራተትንና የአፈር መሸርሸርን ለመቀነስ በታችኛው የኒያባሮንጎ ወንዝ ተፋሰስ ውስጥ ወሳኝ የሆኑ ንኡስ ተፋሰሶች መልሰው እንዲያገግሙ ያደርጋል። ፕሮጀክቱ የደን ልማትን፣ የደን መልሶ ማልማትን፣ የግርናና ደን ልማትንና የከተማን ዛፍ ተከላን ጨምሮ ሥርዓተ-ፆታን ያማከሉና ተፈጥሮ ላይ መሠረት ያደረጉ መፍትሔዎች በማጣመር እነዚህን ስጋቶች በመፍታት የ975,000 ሰዎችን የመቋቋም አቅም ይጨምራል።

ኪጋሊ በሀገሪቱ ወጣ ገባ የመሬት አቀማመጥና ፈጣን የከተማ መስፋፋት እየተባባሰ የመጣ አሳሳቢ የአየር ንብረት አደጋ በተለይም የጎርፍ መጥለቅለቅና የመሬት መንሸራተት አጋጥሟታል። ተፈጥሮ ላይ መሠረት ያደረጉ መፍትሔዎች የሚተገበሩባቸው የኪኩኪሮ፣ ኒያሩገንጌና ጋሳቦ አውራጃዎች ብዙ ቤቶችን ለመሬት መንሸራተትና የታችኛውን ተፋሰስ አካባቢዎች ደግሞ ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ ያደረጉ ገደላማ ቦታዎች አሏቸው፡፡

የሱንካሳ እንቅስቃሴዎች ከሀገር ውስጥ ድርጅቶች ጋር በመተባበር በኒያባሮንጎ ወንዝ ተፋሰስ ውስጥ በአግሮ ደን ልማት፣ በደን ልማትና በደን መልሶ ማልማት ወሳኝ የሆኑ ጥቃቅን ተፋሰሶችን መልሰው እንዲያገግሙ ያደርጋል። በተጨማሪም የመሬት ወረራዎችን በመቆጣጠር ሸለቆዎችን ባሉበት እንዲቆዩና ከፍተኛ ስጋት ያለባቸውን ቤቶች ለመጠበቅ ጥብቅ ጥብቅ የደን ጣቢዎች ይቋቋማሉ።

ተፈጥሮ ላይ መሠረት ያደረጉ መፍትሔዎች እንቅስቃሴዎች በኒያባሮንጎ ወንዝ ተፋሰስ ውስጥ

SUNCASA - Kigali Watershed vertical