Urban Tree Planting Kigali SUNCASA

የከተማ ተፈጥሮ ላይ መሠረት ያደረጉ መፍትሔዎች

የሱንካሳ የተፋሰስ መልሶ ማቋቋምና አረንጓዴ ሥራ የአፍሪካ ከተሞች በአየር ንብረት ተጽእኖዎች በተለይም በጎርፍና በድርቅ ምክንያት የሚፈጠሩና እየተባባሱ የመጡ ተግዳሮቶችን የመቋቋም አቅምን ለማሳደግና የብዝኃ ሕይወትና የሥነ-ምህዳር ጤናን በማጠናከር የመሬትና የውሃ መራቆትን ለመቅረፍ ያለመ ነው።

2/3ኛው የአፍሪካ ከተሞች በእጅጉ ለአየር ንብረት ለውጥ ተፅእኖ የተጋለጡ ሲሆኑ እነዚህ ስጋቶች በተለይ ከፍተኛ ተጋላጭነት ባለባቸው ማኅበረሰቦች ዘንድ እጅግ ከባድ ናቸው። ተፈጥሮ ላይ መሠረት ያደረጉ መፍትሔዎች ለተሻሻለ መላመድና ብዝኃ ህይወት አስተዋፅዖ እያደረጉ የአየር ንብረት አደጋ ተጋላጭነትን ለመቀነስ ወጪ ቆጣቢ የሆኑ ዘዴዎች በመባል ይታወቃሉ።

ሱንካሳ በድሬዳዋ (ኢትዮጵያ)፣ ኪጋሊ (ሩዋንዳ) እና ጆሃንስበርግ (ደቡብ አፍሪካ) በፈጣን የከተሞች መስፋፋት፣ በአዲስ የአየር ንብረት አስተዳደር ሥርዓቶች፣ ደካማ መሠረተ ልማቶች፣ ደካማ ማኅበራዊ-ኢኮኖሚያዊ ችግር ባለባቸው ብዙ ሕዝቦች መኖር ምክንያት  እየጨመረ የመጣውን የአየር ንብረት ተጋላጭነት ለመቅረፍ ያለመ ነው፡፡

የሱንካሳ ለተፈጥሮ ምቹ ንድፍ ዓላማው የመኖሪያ አካባቢዎችንና ግንኙነታቸውን እንዲሁም ሥነ-ምህዳራዊ ቅርፅንና ተግባርን ማሻሻል ነው፡፡ ለመልሶ ማልማትና ለአረንጓዴ ሥራዎች መጤ ያልሆኑ፣ የተለያዩ፣ ከሥነ-ምህዳር ጋር የተጣጣሙና ሁለገብ ዝርያዎችን ይጠቀማል። እነዚህ ተግባራት ጎርፍና የመሬት መንሸራተትን ለመቀነስ እንዲሁም የአፈር መሸርሸርን ለመቆጣጠር የከተማ ሙቀትን ለመቀነስና ብዝኃ ሕይወትን ለመጠበቅ ይረዳሉ፡፡:

ሱንካሳ በየከተሞቹ ያሉ የማዘጋጃ ቤት አስተዳደሮችን፣ የአካዳሚክና የሲቪል ማኅበረሰብ አጋሮችን፣ የሴቶች ድርጅቶችንና ማህበረሰቦችን ቅድሚያ የሚሰጣቸው ተግባራትን የሚመለከት አውድ-ተኮር ተፈጥሮ ላይ መሠረት ያደረገ መፍትሔ በመንደፍ፣ በመተግበር፣ በመከታተልና በመደገፍ ያግዛል። ሱንካሳ የሀገር ውስጥ አጋራ አካላት የአካባቢያዊ የአየር ንብረት መላመድ ግቦችን የሚያሳኩ ውጤታማ ተፈጥሮ ላይ መሠረት ያደረጉ መፍትሔዎችን ለማቅረብ በሚያስችል ደረጃ የሠለጠኑና አቅም ያላቸው መሆናቸውን ለማረጋገጥ ይሠራል።